image
image
image
image
image

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ ተካሄደ::

የካቲት 14-2018, 2018
“የስንዴ ነዶ” የመደመር፣ የአንድነት እና የምርታማነት ምልክት ብቻ ሳይሆን የሕዝባችንን የጋራ ጉልበትና የሥራ ክብር የሚያመለክት ምልክት ነው። የስንዴ ነዶ የሚያሳየው አንድ ነጠላ ጥረት ሳይሆን የተባበረ ጥረት የሚያመጣውን የጋራ ውጤት ነው። ይህ ምልክታችን ሁላችንም በአንድነት በመስራት የጋራ ብልፅግናን እንደምንገነባ እና ሕዝባችንን ከችግር ወደ ብልፅግና እንደምናመጣ ያሳያል። የብልፅግና ፓርቲ ማኒፌስቶ ትናንትን ማከሚያ፣ ዛሬን በአግባቡ መጠቀሚያ፣ ነገን መተለሚያና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት አገር ማሻገሪያ መመሪያችን ነው። የምርጫ መወዳደሪያ ምልክታችን የሆነው የስንዴ ነዶም የመደመር፣ የአንድነት፣ የተባብሮ መሥራት፣ የምርታማነት፣ የተምሳሌትነት፣ የልዕልና እና የሉዓላዊነት መገለጫ ነው። ይህም በሁላችን፣ ከሁላችን፣ ለሁላችን ብልፅግናን የምናረጋግጥበት ምልክታችን ነው። ስለሆነም፣ ብልፅግና ቃሉን ይጠብቃል፤ ቃሉን ይፈጽማል፤ ሕዝቡን የሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት ያደርጋል! #aa_prosperity #Lideta_wereda_6_prosperity_party #ብልፅግናን_ይምረጡ #addisababa #Ethiopiaelection2026 #ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌት_ሀገር

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች