image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 በስድስት ወራት የላቀ ውጤት አስመዘገበ፤ በቀጣይ "በጊዜ የለኝም" መንፈስ ለታላቅ ስኬት መታጨቱ ተገለጸ።

ጥር 4/5/2018, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 በስድስት ወራት የላቀ ውጤት አስመዘገበ፤ በቀጣይ "በጊዜ የለኝም" መንፈስ ለታላቅ ስኬት መታጨቱ ተገለጸ። የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የሁለትዮሽ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማን በዛሬው ዕለት አካሂዷል። በመድረኩም ባለፉት ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች የተገመገሙ ሲሆን፣ ለቀጣይ ስድስት ወራት የሚሆኑ ስልታዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። የወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ ቸኮል እንደገለጹት፣ ባለፉት ስድስት ወራት በሥራ አፈጻጸም የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠል ቀዳሚ ተግባር ነው። በተለይም ከፊታችን የሚጠብቀንን አገራዊ ምርጫ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ልማትን የማስቀጠል ሥራ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል። የታዩ ክፍተቶችን በፍጥነት በማረም በቀጣይ ጊዜያት የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ሁሉም አካል በ"ጊዜ የለኝም" መንፈስ እንዲረባረብም ጥሪ አቅርበዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊና የፖለቲካ አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳምጠው ወንታሞ በበኩላቸው፣ የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የተሻለ ጥረት የታየበት መሆኑን ገልጸዋል። የአገራችንን ብልፅግና ለማረጋገጥ ይህንን ጅምር አጠናክሮ ማስቀጠልና በአንድነት መሥራት እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል። የወረዳው አስተዳደር ምክትል ሥራ አስፈጻሚና የሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ክብሩ ብርቄ፣ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን አንስተዋል። በርካታ ሰው ተኮር ተግባራት የተከናወኑበት ጊዜ መሆኑን ጠቅሰዋል። ለብዙ የወረዳው ነዋሪ ወጣቶች አዳዲስ የሥራ ዕድሎች መፈጠሩና በአገልግሎት አሰጣጥና በመልካም አስተዳደር ዘርፍ የኅብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ሰፊ ጥረት ተመደረጉን ገልጸዋል። ይህ የግምገማ መድረክ ወረዳው የጀመረውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ግልጽ አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን፣ በቀጣይ ወራት ውጤቱን ለማሳደግ የአመራሩና የሠራተኛው ቁርጠኝነት መረጋገጡ ተገልጿል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች