የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ብልጽግና ፓርቲ ዋና ዋና ተግባራት
- በቴክኖሎጂ የታገዘ የክትትልና ድጋፍ ሥርዓት በመዘርጋት የፓርቲና የመንግሥት ዕቅዶች በውጤታማነት እንዲፈጸሙ ማድረግ
- በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃና ዶኩመንቴሽን ሥርዓት መዘርጋትና በቀጣይነት ማሻሻል
- ወቅቱን የዋጀ ሐሳብ በማመንጨት፣ በተከታታይ የአቅም ግንባታ፣ በየጊዜው የሚጋጥሙ ስህተቶችን በማረምና ስኬቶችን በማስቀጠል የፓርቲውን ቀጣይነት ማረጋገጥ
- በአመራሩ፣ በአመራሩና በአባሉ፣ በትውልዶች መካከል ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ማጎልበት
- ወቅቱን የዋጀ ሐሳብ በማመንጨት፣ ስህተቶችን በማረም፣ ስኬቶችን በማስቀጠል የፓርቲውን የመፈጸም አቅም ማሳደግ
- በህብረ-ብሄራዊ ፌደራሊዝም፣ በወልና በነጠላ እዉነት ላይ ቀጣይነት ያለው ውይይት ማድረግ
- ትምህርት ተቋማት ብቁ ዜጋ ማፍራት እንዲችሉና ምሁራን ለሀገር ግንባታ ስኬታማነት የበኩላቸዉን ሚና እንዲወጡ ማስቻል
- በተደራጀ የሕዝብ ተሳትፎና በውጤታማ የአሰራር ሥርዓት የህዝብ አመኔታና እርካታ ማሳደግ
- በግልፅ የተልዕኮ ስኬት ላይ የተመሰረተ የምደባ ስርዓት በመዘርጋት እና የምዘናና እውቅና ስርዓት እውን በማድረግ የፓርቲ ተቋማዊ ጥንካሬ ማሳደግ
- የፓርቲውን አደረጃጀትና አሰራሮች በማዘመን የፓርቲውን ተቋማዊ ጥንካሬ ማሳደግ
- በየደረጃው ያለው አስተባባሪና አመራር ኮሚቴ፣ የአደረጃጀቶች አመራሮች፣ መሰረታዊ ድርጅት፣ ሕዋስ ቋሚ ግንኙነት ጊዜያቸውን ጠብቀው ግምገማና ውይይት ማካሄዳቸውን ማረጋገጥ
- የፓርቲ አደረጃጀቶች፣ አመራሮች፣ አባላት፣ መረጃ በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ የሚተዳደር እንዲሆን ማድረግ
- በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና አሠራር መሰረት ነባሩን አመራርና አባሉን በማጥራት አዳዲስ አባላት ምልመላ በማድረግ የፓርቲውን መሠረት ማስፋት
- በመላ አባላቱ ዘንድ ተቀባይነት ያለው በየደረጃው የውስጥ ምርጫ በማካሔድ የፓርቲውን ዴሞክራሲያዊነትና አመራር ማረጋገጥ
- ጥራትና ብቃት ያላቸውን ዕጩ ለሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በማዘጋጀት የፓርቲውን ተወዳዳሪነት ማሳደግ
- የከተማውን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እቅዶችን በብቃት ማቀድና መፈፀምየሚችል አመራር በየደረጃው ማፍራትና ማብቃት
- ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪል ማህበራት ጋር መርህን የተከተለ ግንኙነት በማጠናከርና ለሀገር ግንባታ ያላቸውን አስተዋፆ በማሳደግ ሀገራዊና ከተማዊ መግባባት ማጠናከር
- ከሲቪል ማህበራት ጋር ግልፅና ተከታታይ የግንኙነት ስርዓት በመዘርጋት ለዲሞክራሲ ባህል ግንባታና ለኢኮኖሚ እድገት ያላቸውን አስተዋፆ አሟጦ መጠቀም
- ለመብቱ የሚታገልና ግዴታውን የሚወጣ የሰለጠነ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚያግዙ የዴሞክራሲ ተቋማትን መገንባት
- የሴቶችና ወጣቶች ሊግ አደረጃጀቶችን በማጠናከር ፖለቲካዊ ተሳትፎና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አበርክቶና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ
- የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ማሳደግ
- የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ
- የወጣቶች ሊግ አደረጃጀቶችን በማጠናከር የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ
- የመደመር ትውልድ መገንባት
- በ2018 እና በ2023 ለሚካሄደው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በቂ ዝግጅት ማካሄድ
- አመራሩ በሚያመነጨው ሀሳብ አባሉና ሌሎች ሰዎች እንዲገዙትና አምነው በፍላጎት እንዲደግፉት መግባባት መፍጠር
- የብዙሃን መገናኛ ዘዴዎች ሽፋን አሟጦ መጠቀም
- በፓርቲ እሳቤዎችንና ስኬቶች ላይ ብቃት ያለው የተግባቦት ሥራ በመሥራት፣ የጋራ ማንነትና የወል እውነቶችን ለመገንባት የሚያግዙ ተቋማትንና ስርዓትን በማጠናከር የትርክት የበላይነት ማሳደግ
- ለአረጋውያን እና ለአቅመ ደካሞችን ቤት መገንባት ለተጠቃሚዎች እንዲተላለፍ ማድረግ
- የፓርቲው የንድፈ ሀሳብ መጽሔት ልሳነ ብልፅግና እንዲታተምና እንዲሰራጭ ማድረግ
- ለፋይናንስ ስራዎች የሚያገለግሉ ሰነዶችና ደረሰኞች እንዲታተሙ ማድረግ
- የፓርቲው ንብረት በአግባቡ ተመዝግቦ እንዲያዝ ማድረግ
- ገቢ እና ወጪ ዕቃዎች አሰራርን በተከተለ አግባብ እንዲፈጸም ማድረግ