image
image
image
image
image

የወረዳ 6 ብልጽግና ፓርቲ የሕብረት አመራሮች በወረዳው የሚከናወኑ የልማትና የኢኒሼቲቭ ሥራዎችን ጎበኙ።

ጥር 6_2018, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ብልጽግና ፓርቲ የሕብረት አመራሮች በወረዳው ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ መጠነ-ሰፊ የልማት ሥራዎችንና ሰው ተኮር የኢኒሼቲቭ ተግባራትን የመስክ ምልከታ አካሄዱ። አመራሮቹ በቆይታቸው በወረዳው ልዩ ትኩረት ተሰጥቶአቸው እየተከናወኑ ያሉ የሚከተሉትን ዋና ዋና ፕሮጀክቶች የነዋሪውን የትራንስፖርት እንግልት የሚቀንሱና የወረዳውን ገጽታ የሚቀይሩ የመንገድ ግንባታዎች። እናቶችን ከቤት ውስጥ ጫና የሚያቃልሉና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ማዕከላትና በኢኒሼቲቭ ደረጃ የተጀመሩና ለተቸገሩ ነዋሪዎች መጠለያ ለመስጠት እየተከናወኑ ያሉ የቤት ዕድሳት ሥራዎች። የብልጽግና ፓርቲ የሕብረት አመራሮች በምልከታው ወቅት እንደገለጹት፤ ወረዳው የጀመራቸው የልማት ሥራዎች የሕዝቡን መሠረታዊ ጥያቄዎች የሚመልሱና "ብልጽግናን በተግባር" የሚያሳዩ ናቸው። በተለይም የኢኒሼቲቭ ሥራዎች ከልማት ባለፈ ለማኅበራዊ ደኅንነትና ለሰው ተኮር ተግባራት ቅድሚያ መስጠታቸው የሚበረታታ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። አመራሮቹ አክለውም፤ እነዚህ የልማት ሥራዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብና ጥራት ተጠናቀቁ ለነዋሪው አገልግሎት እንዲሰጡ ፓርቲው አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል። በጉብኝቱ ወቅት የተገኙ ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ በወረዳው እየታዩ ያሉ የልማት ለውጦች ተስፋ የሚሰጡ መሆናቸውን ገልጸው፣ የብሎክ ካውንስልና የሰላም ኮሚቴዎችም ለልማቱ ስኬታማነት ከጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል። ይህ የመስክ ምልከታ በወረዳው አመራርና በፓርቲው መካከል ያለውን ቅንጅት ያጠናከረ ሲሆን፣ በቀጣይም "በጊዜ የለኝም" መንፈስ የተጀመሩ የኢንሼቲቭ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ የሚያስችል ግልጽ አቅጣጫ የተቀመጠበት ሆኖ ተጠናቋል። ##lideta_wereda_6_prosperity_party

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች