image
image
image
image
image

በወረዳው የስራ እድል ፈጠራ፣ መደበኛ የመንግስት እና የውስጠ ፓርቲ ስራዎች አጠቃላይ አመራር በተገኘበት ተገመገመ።

ጥር 22-2018, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 አስተዳደር ጠቅላላ አመራሮች በተገኙበት የመንግሥትና የፓርቲ ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ። እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት የተገመገሙ ሲሆን፣ በቀሪ ቀናት ትኩረት ለሚሹ ሥራዎች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል። የወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ ቸኮል እንደገለጹት፤ በቀሪ የሥራ ቀናት ውጤታማ ሥራዎችን በውጤታማነት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት መፈጸም ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸው። ሁሌም ትኩረት የሚሹ የሰላምና ጸጥታ ጋር ተያይዞ የብሎኩን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሥራ በልዩ ትኩረት መከናወን እንዳለበት፤ ለወጣቶችና ለሴቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ዮዲት ሰሎሞን እንደተናገሩት አመራሩ ተግባራትን አቀናጅቶና አስተሳስሮ በመስራት የዜጎችን ተጠቀሚነት ማረጋገጥ የአመራር የዘወትር ተግባር በመሆኑ ያሉ ስኬቶችን በማስቀጠል በክፍተት የታዩ ተግባራት ላይ ርብርብ በማድረግ በሁሉም ተግባራት ውጤት ማምጣት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል። በመጨረሻም የመንግሥት እና የውስጠ ፓርቲ ተግባራትን አስተሳስሮ በመምራት ሁሉንም መፈጸም እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች