image
image
image
image
image

"የአሰራር ልዕልና፤ የተደመረ አቅም፣ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል ርዕስ የወረዳ ማጠቃለያ ኮንፈንስ ተካሂዷል።

ታህሳስ 21, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት "የአሰራር ልዕልና፤ የተደመረ አቅም፣ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት!" በሚል ቃል የ2018 ዓ.ም 2ኛ ሩብ ዓመት ኮንፈረንስ አካሄዷል። የልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዮዲት ሰለሞን የወረዳውን ነዋሪ ጥያቄዎች ለመፍታት እና አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት አስተዳደሩ ችግር ፈቺ ተግባራትን ሲሰራ መቆየቱን የገለፁ ሲሆን የአባላት ግንኙነቶችን በማጠናከር ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ም/ኃላፊና ፖለቲካ ዘርፍ አቶ ዳምጠው ወንታሞ በወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት አስተባባሪነት በ6 ወር ውስጥ በርካታ ተግባራት መሠራታቸውን የገለፁ ሲሆን ተሳታፊነትን በማጠናከር ቀጣይ ተግባራትን በጋራ መስራት እንደሚገባ አስተላልፈዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ ቸኮል በበኩላቸው የነዋሪዎችን እንዲሁም የአባላትን ተሳታፊነት በማጠናከር እንደ ወረዳ 6 አስተዳደር የነዋሪውን ተጠቃሚነት የሚያጎሉ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የጋራ ኃላፊነትን መወጣት ይገባል ብለዋል። በወረዳው ብልፅግና ፓርቲ በተዘጋጀው የማጠቃለያ ኮንፈረንስ የወረዳው ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ኃላፊ ወ/ሮ አይቼሽ አዲስ በ2ኛ ሩብ አመት እንዲሁም በመጀመሪያ 6 ወር ውስጥ የተሰሩ ስራዎች ሪፓርት በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን የአባላቱን ተሳታፊነት በመጨመርና ተግባራትን አስተሳስሮ በመስራት ውጤታማ ስራዎች መሠራታቸው ተገልጿል። በመጨረሻም ከተሳታፊ አባላት በተነሱ ሀሳቦች ውይይት በማካሄድ እና ምላሽ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች