በአባላት ላይ በዲሲፕሊን ጉድለት ስለሚወሰዱ እርምጃዎች
ማንኛውም አባል በሚከተሉት ሁኔታዎች ከተግሣጽ ጀምሮ
ከአባልነት እስከ ማሰናበት የሚያደርስ እርምጃ ሊወሰድበት
ይችላል፤
- የፓርቲውን ፕሮግራም፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ውሳኔዎችና
መመሪያዎች ያላከበረ ወይም ሌሎች ጥፋቶችን የፈጸመ
አባል ወይም ዕጩ አባል ጉዳዩ በዝርዝር ታይቶ እንደ
ጥፋቱ ክብደት የዲስፕሊን እርምጃ ይወሰድበታል፤
- ማንኛውም አባል የፓርቲውን የአባልነት መዋጮ
በተከታታይ ለ6 ወራት አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ካልከፈለ
እና ውዝፍ መዋጮውን ለመክፈል ፍቃደኛ ካልሆነ
ከአባልነቱ በራሱ ፈቃድ እንደለቀቀ ይቆጠራል፤
- ማንኛውም አባል በትክክለኛ መረጃ ላይ ሳይመሠረት
አባላትን ከመለመለ ወይም ከአባልነት ካገለለ፣ አባላትን
ከወነጀለ በዲስፕሊን ጥፋት ይጠየቃል፤
- ማንኛውም አመራር ወይም አባል የሐሰት ሪፖርት
መስጠትም ሆነ መጠቀም ክልክል ነው፤
- በፓርቲው ውስጥ አንጃነት እና ቡድንተኝነት መፍጠር
ወይም ማስፋፋት ክልክል ነው፤
- ማንኛውም አባል የሌላ ፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆኑ
ከተደረሰበት ከፓርቲ አባልነቱ ይሰረዛል፤
- ከላይ የተዘረዘሩት እንደተጠበቁ ሆነው በአገሪቱ ህጎች
ጥፋት ተብለው የሚቆጠሩ ድርጊቶችን ፈፅሞ የተገኘ
መሆኑ ሲረጋገጥ በፓርቲው አሠራርም ተጠያቂ ይሆናል፤
የፓርቲው አባላትና ዕጩ አባላት የሚፈጽሟቸው ጥፋቶች
ክብደት እየታየ የሚከተሉት እርምጃዎች ይወሰዳሉ፡-
ለሙሉ አባል፤
- ተግሣጽ፤
- የቃል ማስጠንቀቂያ መስጠት፤
- የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት፤
- ከኃላፊነት ማገድ፤
- ከኃላፊነት ዝቅ ማድረግ፤
- ከኃላፊነት ማንሣት፤
- ከአባልነት ማገድ፤
- ከአባልነት መሠረዝ።