የአባል መብት
ማንኛውም የፓርቲ ሙሉ አባል የሚከተሉት መብቶች
ይኖሩታል፡-
- በፓርቲው አካላት ምርጫዎች የመምረጥና የመመረጥ፤
- በፓርቲው ጉባኤዎች የመሳተፍ፣ በውይይት የመካፈልና
በድምፅ በሚወሰኑ ጉዳዮች ላይ ድምፅ የመስጠት፣
በማንኛውም ጉዳይ ላይ በሕጋዊ መድረኮች ሐሳቡን
በጽሑፍም ሆነ በቃል የማቅረብ፤
- በማንኛውንም የፓርቲ አካል ወይም አባላት ላይ በተቻለ
መጠን በመረጃ የተደገፈ ገንቢ ሂስ የማቅረብ፤
- በየትኛውም የፓርቲ ውሳኔ ቅር ከተሰኘ ቅሬታውን
በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት በየደረጃው ለሚመለከተው
አካል የማቅረብ፤
- ስለራሱ፣ ስለአካል፣ ስለፓርቲው ማወቅ የሚገባውን
ነገር እስከ ፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ የመጠየቅና መልስ
የማግኘት፤
- የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ፣ ፕሮግራም፣ አቋሞችና
ውሳኔዎች ለሌሎች የማሳወቅ፤ የማስተዋወቅ፤ የማሥረጽና
በተጨባጭ እንዲተገበር የማድረግ እና፤
- በየትኛውም ጊዜ በጽሑፍ አመልክቶ እና በእጆቹ የሚገኙ
የፓርቲው ንብረቶችን ኃላፊነት በተሞላበት አግባብ አስረክቦ
ከአባልነት መልቀቅ ይችላል።