የፓርቲው አባል ግዴታዎች
ማንኛውም የፓርቲ አባል የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩበታል፡-
- በማንኛውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ በፓርቲ ሕግ መሠረት የጸደቁትን የፓርቲውን ፕሮግራም፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ መመሪያዎች፣ ውሳኔዎችና ዕቅዶችን የማወቅ፣
- የመቀበል፣ የማክበር፣ የመገዛት እና ለተግባራዊነታቸው በግንባር ቀደምትነት የመታገል፣
- በሚገኝበት የሥራ መስክ እና ኃላፊነት ደረጃ የፓርቲውን አንድነት፣ ጥራትና ጥንካሬ፣ የፓርቲውን የፖለቲካ ዕሳቤዎች ለመጠበቅ ሙሉ ተሳትፎ የማድረግ፣
- የፓርቲውን መርሆዎች፣ ዕሴቶችና የአባላትን የሥነ ምግባር ሕጎችን የማክበር እና የፓርቲውን የህዝብና የሀገርን ደኅንነትና ሉዓላዊነት የመጠበቅ፣
- የሀገሪቱን ሕጎች እና ልዩ ልዩ መንግሥታዊ ውሳኔዎችን ማክበር
- የፓርቲውን አንድነት፣ ጥራትና ጥንካሬ የሚጎዱ ማናቸውንም ዝንባሌዎችና ድርጊቶችን የማጋለጥና የመታገል፣
- በፓርቲው ውስጥ በግለሰቦች ወይም በቡድኖች የተያዙ ተናጠል ዐቋሞችን የፓርቲው በማስመሰል በማናቸውም መልኩ በሚዲያ ከማሠራጨት የመቆጠብ፣
- በአባላት መካከል የሚኖረውን መልካም ግንኙነት ከሚያጎድፍ ድርጊቶች የመታቀብ፣
- በዚህ ደንብ አንቀጽ 18 ንዑስ አንቀጽ 8/ተ/ እንደተገለጸው ማዕከላዊ ኮሚቴ በሚያወጣው የአባልነት መዋጮ ዓይነትና አከፋፈል መመሪያ መሠረት የአባልነት መዋጮ የመክፍል፣
- የፓርቲውን ንብረት በአግባቡ የመጠበቅ፣
- ከሙስና የጸዳ፣ ሙስናንና አድሎአዊ አሠራርን የመታገልና የማጋለጥ ግዴታ እና
- ከአንድ አካባቢ ወይም የሥራ ቦታ ወደ ሌላ አካባቢ ወይም የሥራ ቦታ በቋሚነት ለቅቆ ሲሄድ የለቀቀበትን እና የደረሰበትን የፓርቲ መዋቅር ማሳወቅ፣ የፓርቲውን ንብረት እና ሰነዶችን ለለቀቀበት አካባቢ የፓርቲ መዋቅር ማስረከብ አለበት።